BPDO GOT THE GOLD AWARD!

🏆🏆🏆 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የአዲስ አበባ ታማኝ ግብር ከፋዮች-ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ቃል ድርጅታችን ቤዛ ፖስተርቲ የልማት ድርጅት የወርቅ ደረጃ ሽልማት እንደተበረከተለት በደስታ እንገልፃለን።🏆🏆🏆 ግብር መክፈል የሀገር ፍቅር፣ የዜግነት ሃላፊነት እና ግዴታ አንዱ መገለጫ ነው፡፡ ልማት ያለ ግብር ከግብ አይደርስም ፡፡ታማኝ ግብር ከፋዮች ያሉባት ሀገር ልማት እና ዕድገትም በፍጠነት የመጓዙ ጉዳይ እርግጥ ነው፡፡
በትላንትናው እለት በተካሄደው በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ ዋና ስራ አስፈፃሚያችን አቶ ሰኢድ አህመድ ሽልማቱን ከክቡር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተቀብለዋል። ድርጅታችን በኢትዮጲያ ካሉ ለትርፍ ካልተቋቋሙ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ይህን ሽልማት በማግኘት ብቸኛው መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ኩራት ነው።
✨ ይህ እውቅና ድርጅታችን play your part/ የድርሻችንን እንወጣ የሚለውን መርህ አጉልቶ የሚያሳይ እንዲሁም ማህበረሰቦችን ለማብቃት ብቻ ሳይሆን አገራዊ ኃላፊነትንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው::

We are beyond proud to announce that Beza Posterity Development Organization (BPDO) has been awarded the Gold Award under the “የአዲስ አበባ ታማኝ ግብር ከፋዮቹ የወርቅ ደረጃ ተሸላሚዎች የእውቅና መርሀግብር” by the Addis Ababa City Administration — an outstanding recognition of our organization’s integrity, accountability, and contribution to national development.🏆 BPDO is the ONLY non-governmental, non-profit organization in Ethiopia to ever receive this prestigious award!Our CEO, Mr. Seid Ahmed, proudly accepted the award from Her Excellency Mrs. Adanech Abebe, Mayor of Addis Ababa, during a special recognition ceremony held yesterday.This milestone reflects our long-standing commitment to good governance, transparency, and community transformation.At BPDO, we believe that lasting change begins when everyone “Plays Their Part.”✨ We dedicate this national recognition to all our staff, partners, and communities who continue to make a difference every single day.   https://www.youtube.com/shorts/XLdx_tEoIPg

About The Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

No Related Post